የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ትራንስፖርት ኃላ/የተ/የግል/ማ/ህ ከዚህ በታች የተገለጸውን 261 የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ/ቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | የአንዱ ዋጋ ከቫት
በፊት |
1 | የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12.00R20
የፊት ጎማ- 52 PR 22 ከነከለመንዳሪው Wired tyre/ባለ ሽቦ የኋላ ጎማ – 209 PR 18 ከነከለመንዳሪው Wired tyre/ባለ ሽቦ |
በቁጥር |
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን ጎማ የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 የስራ ቀናት ባምቢስ በሚገኘው የቀድሞ WFP ቢሮ አንደኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ /0925-904380 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ቅጥር ግቢውስጥ የሚግኘው ናሽናል ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል/መ/ማ ስልክ ቁጥር 0996017571/0903014422 ግዢ ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው መጋቢት 1 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚግኘው ናሽናል ትራንስፖርት ኃላ/የተ/የግል/ማ/ህ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 1 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 100,000.00 (መቶ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ለገዢው እቃዎቹን ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው ያላሸነፉ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ወድያወኑ ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊ ንብረቱ ካስረከቡ በዋላ ሲ.ፒ.ኦ. ወድያወኑ ይመለስለታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡